Empowering Ethiopian Investment Professionals with COMFAR Training
- January 27, 2025
- Posted by: admin
- Categories:
No Comments

የጥናት ሰነዱን በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሽፈራው ሰለሞን ለመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ተወካይ አቶ ተከስተ ታደሰ አስረክበዋል። የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሽፈራው በርክክቡ ወቅት እንደገለፁት ፕሮጀክት አገልግሎቱ ያለውን የረጅም ዓመት ልምድ ተጠቅሞ የትልልቅ ተቋማትን ስኬት ለማሳደግና አዳዲሶቹንም ውጤታማ ለማድረግ ሲሰራ መቆየቱን ገልጸው አሁንም መሰቦ ስሚንቶን ወደ ገናናነቱ ለመመለስ የሚያስችል የጥናት ሰነድ አጠናቀው ማስረከባቸውን ገልጸዋል፡፡ የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ተወካይ አቶ ተከስተ ታደሰ በበኩላቸው የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ወደተሻለ ስራ እንዲገባና ወደ ቀድሞ ክብሩ እንዲመለስ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሰራው የአዋጭነት ጥናት አጋዥ መሆኑን ገልጸው በቀጣይም ሙሉ ለሙሉ ወደ ትግበራ እንዲገባ አስፈላጊውን እገዛና ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት በሃገራችን የሚገኙ ትልልቅ ተቋማትን የአዋጭነት ጥናት በመስራት ወደ ትርፋማነት ለመመለስ በትኩረት እየሰራ ያለ ተቋም ሲሆን ባለፉት ጊዜያት የከሰም ፤ ጣና በለስና የፊንጫ ስኳር ፋብሪካዎችን የጥናት ሰነድ አጠናቆ ያስረከበ መሆኑ ይታወሳል፡፡